32 lines
3.1 KiB
Markdown
32 lines
3.1 KiB
Markdown
|
# ጌታ ሆይ፣ በእውነተኛነትህ ለዳዊት የማልክለት የቀድሞው የቃል ኪዳንህ ታማኝነት ወዴት አለ?
|
||
|
|
||
|
ጸሐፊው ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ጌታ ከዳዊት ጋር የገባውን ኪዳን እንዲጠብቅ ለመጠየቅ ነው፡፡"ጌታ ሆይ፣ በቀድሞው ጊዜ እንደ ነበርህ ከዳዊት ጋር የገባኸውን ኪዳን ጠብቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# የቀደመው የቃል ኪዳን ታማኝነትህ ድርጊቶች
|
||
|
|
||
|
"ድርጊቶች" እና "ታማኝነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በግስ እና ተውሳከ ግስ መልካቸው ሊረተጎሙ ይችላሉ፡፡ "አስቀድሞ ያደረግሃቸው ነገሮች አንተ ለቃል ኪዳንህ ታማኝ መሆንህን ያሳያሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# አስታውስ
|
||
|
|
||
|
ጸሐፊው ያህዌን ይህንን እንዲያስትውስ ይጠይቃል፡፡ "አስታውስ" ወይም "ስፍራ ስጠው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# አገልጋችህ መቀለጃ ሆነናል
|
||
|
|
||
|
እዚህ ስፍራ "አገልጋዮችህ" የሚለው የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰዎች ነው፡፡ "እንደምን በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ እንዳፌዙብን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
|
||
|
|
||
|
# እንደምን በልቤ ከአገራት ሁሉ እጅግ ብዙ ስድብን ተሸከምኩ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚወክለው የሰውን ስሜቶች ነው፡፡ "ከአገራት ህዝቦች ብዙ ስድብን ተቋቋምኩ" ወይም "ከየአገራቱ ሰዎች በደረሰብኝ ስድብ ምክንያት ተሰቃየሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ከየአገራቱ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ስፍራ "አገራት" የሚለው የሚወክለው የተለያዩ አገራት ሰዎችን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# የአንተ ጠላቶች ስድብ አወረዱብኝ
|
||
|
|
||
|
ጠላቶች በንጉሱ ላይ በጩኸት መሳደባቸው የተገለጸው ስድብ ጠላቶች በንጉሡ ላይ በሀይል እንደሚወረውሩት ነገር/ቁስ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# አንተ በቀባኸው እርምጃዎች ላይ አፌዙ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ስፍራ "እርምጃዎች" የሚለው የሚወክለው ንጉሡ የሄደበትን ነው፡፡ "የቀባኸውን በሄደበት እየተከተሉ አፌዙበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
|