36 lines
1.6 KiB
Markdown
36 lines
1.6 KiB
Markdown
# አለቆችዋ ከበረዶ ይልቅ ጥሩ፥ ከወተት ይልቅ ነጭ ነበሩ
|
||
|
||
ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1)የእየሩሳሌም መሪዎች ጤነኛ ስለነበሩ ለመመልከት እራሱ የሚያምሩ ነበሩ ወይንም 2)መሪዎችዋ በህሊናቸው እንደ በረዶ ንፁህ እና እንደ ወተት የነጡ ናቸው።
|
||
|
||
# አለቆችዋ
|
||
|
||
“የእየሩሳሌም መሪዎች”
|
||
|
||
# ገላቸው ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ቀይ ነበረ
|
||
|
||
“ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቍ የቀላ” ይሄ ጤንነታቸውን ያመለክታል። “ሰውነታቸው ጤነኛ እና ቀይ ነበረ”
|
||
|
||
# ከቀይ ዕንቍ
|
||
|
||
ጠንካራ ቀይ ከባህር የሚገኝ ለማስጌጥ የሚጠቅም ድንጋይ
|
||
|
||
# ሰንፔር
|
||
|
||
ውድ ሰማያዊ ቀለም ያለው የከበረ ድንጋይ ለማጌጫነት የሚውል።
|
||
|
||
# ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል
|
||
|
||
ይሄ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ፡ 1)የመሪዎቻቸውን ቆዳ ፀሓይ አጥቁሮታል ወይንም 2)እየሩሳሌም ስትቃጠል የነካቸው ጭስ ፊታቸውን አጥቁሯቸዋል።
|
||
|
||
# በመንገድም አልታወቁም
|
||
|
||
በቀጥታ መልኩ ፡ “ማንም አይቶ ሊለያቸው አልቻለም” ሊባል ይችላል።
|
||
|
||
# ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል
|
||
|
||
ከቆዳቸው ሥር ጮማም ሆነ ጡንቻ እንዳልነበረ ያሳያል።
|
||
|
||
# ደርቆአል፤ እንደ እንጨት ሆኖአል
|
||
|
||
የደረቀው ቆዳቸው ከእንጨት ጋር ተመስሏል
|