# አለቆችዋ ከበረዶ ይልቅ ጥሩ፥ ከወተት ይልቅ ነጭ ነበሩ ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1)የእየሩሳሌም መሪዎች ጤነኛ ስለነበሩ ለመመልከት እራሱ የሚያምሩ ነበሩ ወይንም 2)መሪዎችዋ በህሊናቸው እንደ በረዶ ንፁህ እና እንደ ወተት የነጡ ናቸው። # አለቆችዋ “የእየሩሳሌም መሪዎች” # ገላቸው ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ቀይ ነበረ “ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቍ የቀላ” ይሄ ጤንነታቸውን ያመለክታል። “ሰውነታቸው ጤነኛ እና ቀይ ነበረ” # ከቀይ ዕንቍ ጠንካራ ቀይ ከባህር የሚገኝ ለማስጌጥ የሚጠቅም ድንጋይ # ሰንፔር ውድ ሰማያዊ ቀለም ያለው የከበረ ድንጋይ ለማጌጫነት የሚውል። # ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል ይሄ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ፡ 1)የመሪዎቻቸውን ቆዳ ፀሓይ አጥቁሮታል ወይንም 2)እየሩሳሌም ስትቃጠል የነካቸው ጭስ ፊታቸውን አጥቁሯቸዋል። # በመንገድም አልታወቁም በቀጥታ መልኩ ፡ “ማንም አይቶ ሊለያቸው አልቻለም” ሊባል ይችላል። # ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል ከቆዳቸው ሥር ጮማም ሆነ ጡንቻ እንዳልነበረ ያሳያል። # ደርቆአል፤ እንደ እንጨት ሆኖአል የደረቀው ቆዳቸው ከእንጨት ጋር ተመስሏል