1.8 KiB
1.8 KiB
እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺ ወረቀት የታለ?
ከተማዋ እዚያ የነበሩ ሰዎች እናት እንደ ነበረችና ወደ ምርኮ የሰደደቻቸው ከባልዋ የተፋታች ሴት እንደሆነች ያህዌ ስለ ጽዮን ይናገራል፡፡
እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺ ወረቀት የታለ?
ያህዌ ይህን ጥያቄ ያቀረበው እነርሱን ወደ ምርኮ የሰደደበት ምክንያት እንዲሆን ሕዝቡ ‹‹የፍቺውን ወረቀት›› እንዲያቀርቡ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናታችሁን የፈታሁበትን የፍቺ ወረቀት አሳዩኝ››
እናንተን የሸጥኃችሁ ለየትኛው አበዳሪ ነው?
የተሸጡ ይመስል ሕዝቡን ወደ ምርኮ እንደ ሰደደ ያህዌ ይናገራል፡፡
እናንተን የሸጥኃችሁ ለየትኛው አበዳሪ ነው?
ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው የማንም ዕዳ ስለሌለበት እነርሱን አለመሸጡን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ሰዎቹ ግን እንደዚያ አስበው የነበሩ ይመስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የማንም ዕዳ ስለሌለብኝ እናንተን አልሸጥሁም››
ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኃል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈትታለች
ያህዌ ሕዝቡን ወደ ምርኮ የሰደደበትን ምክንያት ይናገራል፤ እነርሱ የተሸጡትና እናታቸውም የተፈታችው በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ኀጢአታችሁ ሸጥኃችሁ፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁን ፈታሁ››