20 lines
1.8 KiB
Markdown
20 lines
1.8 KiB
Markdown
|
# እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺ ወረቀት የታለ?
|
||
|
|
||
|
ከተማዋ እዚያ የነበሩ ሰዎች እናት እንደ ነበረችና ወደ ምርኮ የሰደደቻቸው ከባልዋ የተፋታች ሴት እንደሆነች ያህዌ ስለ ጽዮን ይናገራል፡፡
|
||
|
|
||
|
# እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺ ወረቀት የታለ?
|
||
|
|
||
|
ያህዌ ይህን ጥያቄ ያቀረበው እነርሱን ወደ ምርኮ የሰደደበት ምክንያት እንዲሆን ሕዝቡ ‹‹የፍቺውን ወረቀት›› እንዲያቀርቡ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናታችሁን የፈታሁበትን የፍቺ ወረቀት አሳዩኝ››
|
||
|
|
||
|
# እናንተን የሸጥኃችሁ ለየትኛው አበዳሪ ነው?
|
||
|
|
||
|
የተሸጡ ይመስል ሕዝቡን ወደ ምርኮ እንደ ሰደደ ያህዌ ይናገራል፡፡
|
||
|
|
||
|
# እናንተን የሸጥኃችሁ ለየትኛው አበዳሪ ነው?
|
||
|
|
||
|
ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው የማንም ዕዳ ስለሌለበት እነርሱን አለመሸጡን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ሰዎቹ ግን እንደዚያ አስበው የነበሩ ይመስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የማንም ዕዳ ስለሌለብኝ እናንተን አልሸጥሁም››
|
||
|
|
||
|
# ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኃል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈትታለች
|
||
|
|
||
|
ያህዌ ሕዝቡን ወደ ምርኮ የሰደደበትን ምክንያት ይናገራል፤ እነርሱ የተሸጡትና እናታቸውም የተፈታችው በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ኀጢአታችሁ ሸጥኃችሁ፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁን ፈታሁ››
|