am_tn/psa/074/018.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

አሳፍ የእግዚአብሔርን እርዳታ እየጠየቀ ነው፡፡

አስብ

“ትኩረት ስጥ፡፡” ይህ በ መዝሙረ ዳዊት 74:2 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠላት በአንተ ላይ ስድብን አወረደ

አሳፍ ስለ ስድብ ቃላቶች ሲናገር ጠላት በእግዚአብሔር እንደሚወረውረው እንደ ድንጋይ ቁሳዊ ነገር እንደሆነ ተደርጎ ተገልጧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላት አንተን ብዙ ጊዜ ሰደበህ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የርግብህን ህይወት

አሳፍ ስለ ራሱ ማንም ረዳት እንደሌላት ወፍ እንደ ርግብ አድርጎ ተናግሯል፡፡ ይህ ሀረግ ለእስራኤል ህዝብ ምናልባት ተለዋጭ ዘይቤ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ፣ የአንተ ርግብ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ርግብ

ራስዋን መከላከል የማትችልና እንደ ለማዳ እንስሳ የምትጠበቅ ትንሽ ወፍ ናት፡፡

የዱር እንስሳ

ይህ ምናልባት ለእስራኤል ጠላት ተለዋጭ ዘይቤ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ዱር እንስሳ የመሰለ ጨካኝ ጠላት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የችግረኞች ህዝብህን ህይወት ለዘላለሙ አትርሳ

“የተቸገሩ ህዝብህን ለመርዳት ምንም ነገር ካለማድረግ ለዘላለል አትቀጥል፡፡” ይህ በአዎንታዊ ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተቸገሩ ህዝብህን ለመርዳት በፍጥነት ና” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)