am_tn/psa/035/021.md

36 lines
2.1 KiB
Markdown

# አፋቸውን አስፍተው የከፈቱት ጸሐፊውን ለመክሰስ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣
‹‹እኔን ለመክሰስ ጮኹብኝ››
# አሃ፣ አሃ
ይህ አንድነ ነገር በድንገት ሲታይ ወይም ግልጽ ሲሆን የሚባል ቃለ አጋኖ ነው፤ ለሚከተለው ዐረፍተ ነገር አጽንዖት ይሰጣል፡፡
# በዐይናችን ዐየነው
‹‹ዐይናችን›› የሚያመለክተው የጠላቶቹን ዐይን ነው፡፡ እንዲህ ያሉት ጸሐፊው አንዳች መጥፎ ነገር ሲያደርግ ስላዩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐየነው›› ወይም ያደረግኸውን መጥፎ ነገር ዐየን››
# አንተ አይተሃልና
‹‹ያየው›› የጸሐፊው ጠላቶችን ሐሰተኛ ክስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሐሰት እየከሰሱኝ እንደሆነ ዐየህ››
# ዝም አትበል
‹‹ያደረጉትን ቸል አትበል›› ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባደረጉት መሠረት ፍረድባቸው››
# ከእኔ አትራቅ
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ እኔ ቅረብ››
# ተነሥ፣ ንቃ
እንዲህ ማለት እግዚአብሔር ተኝቶአል ማለት አይደለም፡፡ ጸሐፊው እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ ይፈልጋል፡፡ ሁለቱም ቃሎች ተመሳሳይ ቢሆኑም የልመናውን አጣዳፊነት አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ያንቀላፋህ ይመስለኛል! ንቃ››
# ልትከራከርልኝ
‹‹መከራከር›› የሚለውን የነገር ስም፣ ‹‹ተከራከር›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ ተከራከር››
# ነገሬን
ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ››