am_tn/psa/035/021.md

2.1 KiB

አፋቸውን አስፍተው የከፈቱት ጸሐፊውን ለመክሰስ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣

‹‹እኔን ለመክሰስ ጮኹብኝ››

አሃ፣ አሃ

ይህ አንድነ ነገር በድንገት ሲታይ ወይም ግልጽ ሲሆን የሚባል ቃለ አጋኖ ነው፤ ለሚከተለው ዐረፍተ ነገር አጽንዖት ይሰጣል፡፡

በዐይናችን ዐየነው

‹‹ዐይናችን›› የሚያመለክተው የጠላቶቹን ዐይን ነው፡፡ እንዲህ ያሉት ጸሐፊው አንዳች መጥፎ ነገር ሲያደርግ ስላዩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐየነው›› ወይም ያደረግኸውን መጥፎ ነገር ዐየን››

አንተ አይተሃልና

‹‹ያየው›› የጸሐፊው ጠላቶችን ሐሰተኛ ክስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሐሰት እየከሰሱኝ እንደሆነ ዐየህ››

ዝም አትበል

‹‹ያደረጉትን ቸል አትበል›› ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባደረጉት መሠረት ፍረድባቸው››

ከእኔ አትራቅ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ እኔ ቅረብ››

ተነሥ፣ ንቃ

እንዲህ ማለት እግዚአብሔር ተኝቶአል ማለት አይደለም፡፡ ጸሐፊው እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ ይፈልጋል፡፡ ሁለቱም ቃሎች ተመሳሳይ ቢሆኑም የልመናውን አጣዳፊነት አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ያንቀላፋህ ይመስለኛል! ንቃ››

ልትከራከርልኝ

‹‹መከራከር›› የሚለውን የነገር ስም፣ ‹‹ተከራከር›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ ተከራከር››

ነገሬን

ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእኔ››