am_tn/pro/05/11.md

1.6 KiB

ስጋህ እና ሰውነትህ መነመነ

“ስጋ” እና “ሰውነት” የሚሉት ቃሎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው እናም የሰውን ሁለንተና ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰውነትህ መነመነ” ወይም “አንተ መነመንህ” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

መነመነ

“በሰውነት አካል መድከም” ወይም “ደካማ እና ጤና የጎደለው መሆን”

ተግሳፅን ጠላሁ…….. ልቤ እርማትን ናቀ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ሀሳብን ይገልፃሉ እናም ምን ያህል ይህ ሰው አስተማሪው የነገረውን ነገር እንደጠላ ያስገነዝባል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ተግሳፅን እንዴት ጠላሁ

“እንዴት” የሚለው ቃል የጥላቻውን ብርታት የሚያጎላ ቃለ አጋኖ ነው፡፡ ተግሳፅ የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ሲገስፀኝ በጣም እጠላለሁ” (ቃለ አጋኖ እና ረቂቂ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ ተግሳጽን ጠላ

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ሰውየውንና ስሜቶቹን ይወክላል፡፡: “ተግሳጽ” የሚለው ቃል በግስ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ተርጉም፡- “ሰዎች ሲገስጹኝ ጠላኋቸው” (ተዛምዶአዊ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልቱ)