# ስጋህ እና ሰውነትህ መነመነ “ስጋ” እና “ሰውነት” የሚሉት ቃሎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው እናም የሰውን ሁለንተና ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰውነትህ መነመነ” ወይም “አንተ መነመንህ” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ) # መነመነ “በሰውነት አካል መድከም” ወይም “ደካማ እና ጤና የጎደለው መሆን” # ተግሳፅን ጠላሁ…….. ልቤ እርማትን ናቀ እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ሀሳብን ይገልፃሉ እናም ምን ያህል ይህ ሰው አስተማሪው የነገረውን ነገር እንደጠላ ያስገነዝባል፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ) # ተግሳፅን እንዴት ጠላሁ “እንዴት” የሚለው ቃል የጥላቻውን ብርታት የሚያጎላ ቃለ አጋኖ ነው፡፡ ተግሳፅ የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድ ሰው ሲገስፀኝ በጣም እጠላለሁ” (ቃለ አጋኖ እና ረቂቂ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) # ልቤ ተግሳጽን ጠላ እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ሰውየውንና ስሜቶቹን ይወክላል፡፡: “ተግሳጽ” የሚለው ቃል በግስ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ተርጉም፡- “ሰዎች ሲገስጹኝ ጠላኋቸው” (ተዛምዶአዊ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልቱ)