am_tn/pro/01/01.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ቁጥር 2-33 ግጥም ነው፡፡ (ግጥም የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብን እና ተግሳፅን ለማስተማር

ይህን ለውጦ “ጥበብ” እና “ተግሳፅ” የተባሉት ረቂቅ ስሞችን እንደ ገላጭ ወይም ግስ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- እንዴት ጥበበኛ መሆን እንደሚቻል እናንተን ለማስተማር እና እንዴት ግብረገባዊ ህይወት መኖር እንደሚቻል አቅጣጫ ለማሳየት ነው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አርቆ ለማስተዋል የሚያስችሉ ቃላትን ለማስተማር

“ጥበበኛ አስተምህሮዎችን እንድትረዱ ለማገዝ”

ስለዚህ እናንተ እንድትቀበሉ

እዚህ ላይ “እናንተ” የሚመለከተው አንባቢዎችን ነው፡፡ በእናንተ ቋንቋ የተለመደ ከሆነ “እኛ” በሚለው አካታች ቃል መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ እኛ እንድንቀበል” (የሁለተኛ መደብ ቅርጾችን እና አካታች “እኛ” ይመልከቱ)

ለመኖር የሚያስችል መመሪያ ለመቀበል

ይህን ለውጦ “መመሪያ” የሚለው ረቂቅ ስምን እንደ ግስ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዴት መኖር እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)