am_tn/pro/01/01.md

20 lines
1.6 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አጠቃላይ መረጃ፡-
ቁጥር 2-33 ግጥም ነው፡፡ (ግጥም የሚለውን ይመልከቱ)
# ጥበብን እና ተግሳፅን ለማስተማር
ይህን ለውጦ “ጥበብ” እና “ተግሳፅ” የተባሉት ረቂቅ ስሞችን እንደ ገላጭ ወይም ግስ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- እንዴት ጥበበኛ መሆን እንደሚቻል እናንተን ለማስተማር እና እንዴት ግብረገባዊ ህይወት መኖር እንደሚቻል አቅጣጫ ለማሳየት ነው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
# አርቆ ለማስተዋል የሚያስችሉ ቃላትን ለማስተማር
“ጥበበኛ አስተምህሮዎችን እንድትረዱ ለማገዝ”
# ስለዚህ እናንተ እንድትቀበሉ
እዚህ ላይ “እናንተ” የሚመለከተው አንባቢዎችን ነው፡፡ በእናንተ ቋንቋ የተለመደ ከሆነ “እኛ” በሚለው አካታች ቃል መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለዚህ እኛ እንድንቀበል” (የሁለተኛ መደብ ቅርጾችን እና አካታች “እኛ” ይመልከቱ)
# ለመኖር የሚያስችል መመሪያ ለመቀበል
ይህን ለውጦ “መመሪያ” የሚለው ረቂቅ ስምን እንደ ግስ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዴት መኖር እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)