am_tn/num/14/31.md

1.4 KiB

በድኖቻችሁ ይወድቃሉ

የበድኖቻቸው መውደቅ የሚያመለክተው የሚሞቱ መሆኑን ነው፡፡“ትሞታላችሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ልጆቻችሁ በምድረ በዳ እረኞች ይሆናሉ

አንዳንድ የትርጉም ቅጂዎች “ልጆቻችሁ በምድረ በዳ ይቅበዘበዛሉ”የሚለውን ሃሣብ ይመርጡታል፡፡ይሄ የሆነበት ምክኒያት ከብቶቹ የሚግጡት ሣር እስከሚያገኙ ድረስ እረኞቹ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ ስለነበረ ነው፡፡

የሥራችሁን ውጤት መሸከም ይኖርባቸዋል

“ከድርጊታችሁ ፍሬ የተነሣ ሊሰቃዩ ይገባል”ወይም “ከእናንተ ድርጊት የተነሣ እነርሱ ሊሰቃዩ ይገባል”

በድኖቻችሁ እስከጠፉ ድረስ

በድን ሬሣ ነው፡፡በድኖቻችሀ እስኪጠፉ ድረስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ሰው ሣይቀር የሚሞት መሆኑን ነው፡፡“ከእናንተ የመጨረሻው ሰው እስከሚሞት ድረስ”ወይም “ሁላችሁም እስክትሞቱ ድረስ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)