am_tn/nam/02/08.md

28 lines
2.5 KiB
Markdown

# ነነዌ እንደሚያፈስ የኩሬ ውሃ ናት፣ ሕዝቧም እንደ ውሃ ፈሳሽ ይሸሻል
ናሆም ሕዝቡ ከነነዌ ከተማ የሚሸሽበትን ሁኔታ ግድብ በሚፈርስበት ጊዜ ውሃው ከማከማቻው ጎርፎ ከመውረዱ ጋር ያነጻጽረዋል። (ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት)
# ብሯን በዝብዙ. . . የነነዌን የተዋቡ ነገሮች
እዚህ ጋ ተናጋሪው ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ይህ ምናልባት ናሆም ለተዋጊዎቹ አቅጣጫ የሚሰጥበት ይሆን ይሆናል ወይም ምናልባት ተዋጊዎቹ ለእርስ በእርሳቸው አቅጣጫ የሚሰጡበትና የሚነጋገሩበት ሊሆን ይችላል። (ምናባዊውን ሰው መናገር የሚለውን ተመልከት)
# ብሩን በዝብዙ፣ ወርቁን በዝብዙ
“በዝብዙ” የሚለው ቃል በማስገደድ የሚሰረቁ ነገሮች፣ አብዛኛውን ጊዜ በጦርነት ወቅት ማለት ነው። አ.ት፡ “ብሩን በብዝበዛ ውሰዱ፣ ወርቁን በብዝበዛ ውሰዱ” ወይም ”ብሩን ውሰዱ፣ ወርቁን ውሰዱ”
# ለእርሱም ማብቂያ የለውም
“ማብቂያ የለውም” የሚሉት ቃላት አንድ ነገር በብዛት መኖሩን ለመግለጽ የተነገረ ግነት ነው። አ.ት፡ “እጅግ ብዙ አለ” (ግነት እና ማጠቃለያ የሚሉትን ተመልከት)
# የነነዌ የተዋቡ ነገሮች ክብር ሁሉ
ይህ ሐረግ በነነዌ የነበረውን ብር፣ ወርቅ፣ እና ሌሎች ሀብቶች ያመለክታል። ግሱ ምናልባት ቀደም ካለው ሐረግ ሊወሰድ ይችላል። አ.ት፡ “ለነነዌ የተዋበ ሀብት ሁሉ ለክብሩ ማብቂያ የለውም” ( መግደፍ የሚለውን ተመልከት)
# የእያንዳንዱ ልብ ይቀልጣል
ናሆም ልክ ልባቸው እንደ ሰም የቀለጠ ይመስል ሕዝቡ አቅም እንዳጣ ይናገራል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ አቅም አጥቷል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# የእያንዳንዱ ጉልበት ይብረከረካል
ይህ በታላቅ ፍርሃት ምክንያት የሚፈጠረውን አካላዊ ምላሽ ያሳያል። የሕዝቡ እግር ያለ መጠን በመንቀጥቀጡ ጉልበቶቻቸው ስለሚጋጩ መራመድም ሆነ መሮጥ አይችሉም።