am_tn/nam/02/08.md

2.5 KiB

ነነዌ እንደሚያፈስ የኩሬ ውሃ ናት፣ ሕዝቧም እንደ ውሃ ፈሳሽ ይሸሻል

ናሆም ሕዝቡ ከነነዌ ከተማ የሚሸሽበትን ሁኔታ ግድብ በሚፈርስበት ጊዜ ውሃው ከማከማቻው ጎርፎ ከመውረዱ ጋር ያነጻጽረዋል። (ተነጻጻሪ የሚለውን ተመልከት)

ብሯን በዝብዙ. . . የነነዌን የተዋቡ ነገሮች

እዚህ ጋ ተናጋሪው ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ይህ ምናልባት ናሆም ለተዋጊዎቹ አቅጣጫ የሚሰጥበት ይሆን ይሆናል ወይም ምናልባት ተዋጊዎቹ ለእርስ በእርሳቸው አቅጣጫ የሚሰጡበትና የሚነጋገሩበት ሊሆን ይችላል። (ምናባዊውን ሰው መናገር የሚለውን ተመልከት)

ብሩን በዝብዙ፣ ወርቁን በዝብዙ

“በዝብዙ” የሚለው ቃል በማስገደድ የሚሰረቁ ነገሮች፣ አብዛኛውን ጊዜ በጦርነት ወቅት ማለት ነው። አ.ት፡ “ብሩን በብዝበዛ ውሰዱ፣ ወርቁን በብዝበዛ ውሰዱ” ወይም ”ብሩን ውሰዱ፣ ወርቁን ውሰዱ”

ለእርሱም ማብቂያ የለውም

“ማብቂያ የለውም” የሚሉት ቃላት አንድ ነገር በብዛት መኖሩን ለመግለጽ የተነገረ ግነት ነው። አ.ት፡ “እጅግ ብዙ አለ” (ግነት እና ማጠቃለያ የሚሉትን ተመልከት)

የነነዌ የተዋቡ ነገሮች ክብር ሁሉ

ይህ ሐረግ በነነዌ የነበረውን ብር፣ ወርቅ፣ እና ሌሎች ሀብቶች ያመለክታል። ግሱ ምናልባት ቀደም ካለው ሐረግ ሊወሰድ ይችላል። አ.ት፡ “ለነነዌ የተዋበ ሀብት ሁሉ ለክብሩ ማብቂያ የለውም” ( መግደፍ የሚለውን ተመልከት)

የእያንዳንዱ ልብ ይቀልጣል

ናሆም ልክ ልባቸው እንደ ሰም የቀለጠ ይመስል ሕዝቡ አቅም እንዳጣ ይናገራል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ አቅም አጥቷል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእያንዳንዱ ጉልበት ይብረከረካል

ይህ በታላቅ ፍርሃት ምክንያት የሚፈጠረውን አካላዊ ምላሽ ያሳያል። የሕዝቡ እግር ያለ መጠን በመንቀጥቀጡ ጉልበቶቻቸው ስለሚጋጩ መራመድም ሆነ መሮጥ አይችሉም።