am_tn/mic/01/13.md

1.7 KiB

X

ለኪሶ “ለኪሶ” የሚለው ስም በዕብራይስጥ “ለሰረገሎቹ” ከሚለው ድምፅ ጋር ይመሳሰላል። ሕዝቡ ለውጊያ ሳይሆን ለመሸሽ ሰረገላዎቻቸውን ያስጋልባሉ። ለኪሶ በይሁዳ ከምትኖረው ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ እጅግ አስፈላጊ ከተማ ነበረች።

የጽዮን ሴት ልጅ “ሴት ልጅ” የሚለው ቃል ለከተማይቱ ሰዎች የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የጽዮን ሕዝብ” ወይም “በጽዮን የሚኖረው ሕዝብ”።

የእስራኤል መተላለፍ በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ እንዳደረጉት አልታዘዝ ብላችኋል”።

ሞሬሼትጌት “ ‘ሞሬሼት’ የሚለው ስም ትርጉም ‘መለየት’ ማለት ነው የሚለውን በግርጌ ማስታወሻ ላይ መጨመር ያስፈልግህ ይሆናል። በተጨማሪም ‘ዕጮኛ’ ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው”። በዚህ ዘይቤአዊ አነጋገር ሞሬሼት አሦር የሚወስዳት ሙሽሪት ስትሆን የ “መሰናበቻ ስጦታ”ው ወደ ትዳሯ ይዛው እንድትሄድ ቤተ ሰቦቿ የሚሰጧት ስጦታ ነው።

አክዚብ “የዚህች ከተማ ስም በዕብራይስጥ “አታላይ ነገር” ከሚለው አገላለጽ ጋር ፍጹም ተመሳሳይነት አለው” በማለት በግርጌ ማስታወሻ ላይ ልትጨምረው ያስፈልግህ ይሆናል።