17 lines
1.7 KiB
Markdown
17 lines
1.7 KiB
Markdown
|
# X
|
||
|
|
||
|
ለኪሶ
|
||
|
“ለኪሶ” የሚለው ስም በዕብራይስጥ “ለሰረገሎቹ” ከሚለው ድምፅ ጋር ይመሳሰላል። ሕዝቡ ለውጊያ ሳይሆን ለመሸሽ ሰረገላዎቻቸውን ያስጋልባሉ። ለኪሶ በይሁዳ ከምትኖረው ከኢየሩሳሌም ቀጥሎ እጅግ አስፈላጊ ከተማ ነበረች።
|
||
|
|
||
|
የጽዮን ሴት ልጅ
|
||
|
“ሴት ልጅ” የሚለው ቃል ለከተማይቱ ሰዎች የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የጽዮን ሕዝብ” ወይም “በጽዮን የሚኖረው ሕዝብ”።
|
||
|
|
||
|
የእስራኤል መተላለፍ በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና
|
||
|
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ እንዳደረጉት አልታዘዝ ብላችኋል”።
|
||
|
|
||
|
ሞሬሼትጌት
|
||
|
“ ‘ሞሬሼት’ የሚለው ስም ትርጉም ‘መለየት’ ማለት ነው የሚለውን በግርጌ ማስታወሻ ላይ መጨመር ያስፈልግህ ይሆናል። በተጨማሪም ‘ዕጮኛ’ ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው”። በዚህ ዘይቤአዊ አነጋገር ሞሬሼት አሦር የሚወስዳት ሙሽሪት ስትሆን የ “መሰናበቻ ስጦታ”ው ወደ ትዳሯ ይዛው እንድትሄድ ቤተ ሰቦቿ የሚሰጧት ስጦታ ነው።
|
||
|
|
||
|
አክዚብ
|
||
|
“የዚህች ከተማ ስም በዕብራይስጥ “አታላይ ነገር” ከሚለው አገላለጽ ጋር ፍጹም ተመሳሳይነት አለው” በማለት በግርጌ ማስታወሻ ላይ ልትጨምረው ያስፈልግህ ይሆናል።
|