am_tn/mat/06/01.md

2.0 KiB

ማቴዎስ 6፡1-2

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ በ MAT 5:3ላይ የተጀመረውን የተራራው ስብከቱን ማስተማር ቀጥሏል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “የጽድቅን ተግባራት” የሆኑትን አስራት ማውጣት፣ ጸሎት እና ጾምን አስመልክቶ አስምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃል ሁሉም በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ በሰዎች ለመታየት ለሰዎች ብለው የሚያደርጉ ሰዎች እርሱን እያከበሩት እንዳልሆነ በተዘዋዋር መልኩ ያመለክታል፡፡ ይህ እንዲህ ባለ መልኩ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ስላደጋችሁት ነገር ሰዎች ያመሰግናችሁ ዘንድ በሰዎች ፊት የሚታደርጉት ከሆነ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-explicit]] እና [[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/guidelines-sonofgodprinciples]] ተመልከት) ለራስህ መለከት አታስነፋ ይህ ምሳሌ የሚያሳየው የሰዎችን ትኩረት ሆን ብለህ ለመሳብ የተለያዩ ነገሮችን ማድረግ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በብዙ ሰዎች መካከል መለከት በታላቅ ድምፅ እንደሚነፋ ሰው ወደ ራሰህ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ጥረት አታድረግ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) እውነት እልሃለሁ “እውነቱን እነግርሃለሁ”፡፡ ይህ ሀረግ ኢየሱስ በመቀጠል ስለሚናገረው ነገር አጽኖት የሚሰጥ ሀረግ ነው፡፡