am_tn/mat/05/01.md

2.1 KiB

ማቴዎስ 5፡1-4

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ይህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማስመተማር የጀመረበት አዲስ ታሪክ ጅማሬ ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍል እስከ ምዕራፍ 7 ድረስ ይቀጥላል እንዲሁም ብዙ ጊዜም የተራራው ስብከት ተብሎ ይጠራል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 3 ላይ ኢየሱስ የተባረኩ ሰዎች ባሕርያት ምን ምን እንደሆኑ መግለጽ ይጀምራል፡፡

አፉን ከፍቶ ኤቲ፡ “ኢየሱስ መናገር ጀመረ” (rc://*/ta/man/translate/figs-idiom ተመልከት)

አስተማራቸው “እነርሱን” የሚለው ቃል ደቀ መዛሙርቱን የሚያመለክት ነው፡፡

በመንፈሰስ ድሆች ይህ ማለት ትሁት የሆነ ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር እንደሚያስፈልጋቸው ያወቁ፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-idiom ተመልከት)

መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና በዚህ ሥፍራ ላይ “መንግስተ ሰማየት” የሚያመለክተው እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ መግዛቱን፡፡ ይህ ሀረግ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው፡፡ ከተቻለ በትርጉማችሁ ውስጥ “ሰማይ” የሚለው ቃል እንዲኖር አድርጉ፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ ያለው እግዚአብሔር ንጉሣቸው ይሆናልና፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-metonymy ተመልከት)

የሚያለቅሱ ያዘኑበት ምክንያት ሊሆን የሚችለው 1) በዚህ ዓለም ኃጢአት ወይም 2) በራሳቸው ኃጢአት ወይም 3) በሌላ ሰው ሞት ምክንያት፡፡ ቋንቋችሁ ካላስገደዳችሁ በስቀተር ምክንያቱን አትግለጹ፡፡

ይጽናናሉና ይህ እንዲህ በቀጥታ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ያጽናናቸዋል፡፡” (rc://*/ta/man/translate/figs-activepassive ተመልከት)