am_tn/mat/05/38.md

2.1 KiB

ማቴዎስ 5፡38-39

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሩ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ጠላትን ስለመበቀል ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ሰምታችኋል” እና “እኔ እንዲህ እላችኋለሁ” በሚለው ሀረግ ውስጥ የሚገኘው “እናንተ” የሚለው ቃል የተገለጸው በብዙ ቁጥር ነው፡፡ “ማንም ቢመታህ” የሚለው ሀረግ ውስጥ የሚገኘው “አንተ” የሚለው ቃል ግን በብዙ ቁጥር መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ (rc://*/ta/man/translate/figs-you ተመልከት) እንዲህ መባሉን ሰምታችኋል ይህንን በ MAT 5:33 እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከት፡፡ ዐይን ለዐይን ጥርስ ለጥርስ የሙሴ ሕግ የጎዳንን ሰው በተመሳሳይ መንገድ እንዲጎዳ ያዛል ይሁን እንጂ ከዚያ በላይ እንዲጎዳ አያደርግም፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላለሁ ይህንን በ MAT 5:22.እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከት፡፡ ክፉውን “ክፉ የሆነ ሰው” ወይም “የጎዳችሁ ሰው” (UDB) ቀኝ ጉንጫችሁን የመታችሁ ኢየሱስ በኖረበት ባሕል ውስጥ የአንድን ሰው ቀኝ ጉንጭ በጥፊ መምታት ስድብ ነው፡፡ ልክ እንደ ዐይን እና እጅ ሁሉ ቀኝ ጉንጭም በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ጉንጭን በጥፊ መምታት ትልቅ ስድብ ነው፡፡ መምታት “በጥፊ መምታት”፡፡ ይህ ማለት በቃሪያ ጥፉ አንድን ሰው መምታት ማለት ነው፡፡ ሌላኛውንም ፊት አዙሩለት “ሌላኛውን ፊታችሁን የሚታችሁ ዘንድ አዙሩለት”