am_tn/mat/05/33.md

4.0 KiB

ማቴዎስ 5፡33-35

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሩ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ስለመሃላ ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ሰምታችኋል በሚለው ሀረግ ውስጥ ያለው “እናንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ይሁን እንጂ “አትማል” እና “ፈጽማቸው” በሚለው ውስጥ ያለው “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ እንደገና አንተ “አንተም ደግሞ” ወይም “ሌላ ምሳሌ ይኼው፡፡ አንተ” እንዲህ ሲባል ሰምታችኋል . . . በውሸት አትማሉ በዚህ ሥፍራ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ጋር በግልጽ የሚስማማ ነገር ስናገር ትመለከታላችሁ፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎችን ለማሳመን የእነርሱ ያልሆነ ነገር እንዳይናገሩ ያሳስባቸዋል፡፡ ኤቲ፡ “የሃይማኖት መሪዎቻችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለው ነግረዋችኋል . . . አትማሉ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) በውሸት አትማሉ መኃላችሁን ፈጽሙ እንጂ አማራጭ ትርጉሞች 1) የማትፈጽሙትን ነገር አደርጋለሁ ብላችሁ በእግዚአብሔር ፊት አትማሉ ወይም 2) አንድ ነገር ውሸት መሆኑን እያወቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት እውነት ነው ብላችሁ አትማሉ፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ በ MAT 5:22 የሚገኘውን በምን መንገድ እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ ፈጽሞ አትማሉ . . . የታላቁ ንጉሥ ከተማ በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ የተናገረው ማንም ሰው ፈጽሞ መማል እንዳሌለበት ነው፡፡ አንዳንዶች አንድ ሰው የማለው ከእግዚአብሔር ውጪ በሆነ ነገር ማለትም በሰማይ፣ በምድር ዌም በኢየሩሳም የማለ ከሆነ መሃላውን ሳይፈጽም ቢቀር ይህን ያኽል ጉዳት የለውም ብለው ሳያስተምሩ አልቀሩም፡፡ ኢየሱስ ይህም ቢሆን እንደ ማንኛውም መሃላ መጥፎ ነው ምክንያቱም ሁሉ ነገር የእግዚአብሔር ስለሆነ ነው፡፡ ፈጽሞ አትማሉ ለዚህ ትዕዛዝ የሚሆን ቃል በቋንቋችሁ በብዙ ቁጥር የሚገኝ ከሆነ በዚህ ሥፍራ ይህንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ “በውሸት አትማሉ” የሚለው ሀረግ አድማጮች መማል እንደሚቻል ነገር ግን በውሸት መማል የማይቻል እንደሆነ ያሳያል፡፡ “ፈጽሞ አትማሉ” የሚለው ሀረግ ግን ሁሉንም ዓይነት መሃላዎችን ይከለክላል፡፡ የእግዚአብሔር ዚፋን ነው በዚህ ሥፍራ ላይ “ዙፋን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ መግዛቱን ነው፡፡ ኤቲ፡ “የእግዚአብሔር አገዛዝ”፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት) የእግሩ መረገጫ ናት ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ምድርም ቢትሆን የእግዚአብሔር መሆኗን ያሳያል፡፡ ኤቲ፡ “ንጉሥ እግሩን የሚያሳርፍበት የእግሩ መርገጫ ሥፍራ ዓይነት ናት፡፡ (rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor ተመልከት) የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና “ይህች ከተማ የታላቁ ንጉሥ የእግዚአብሔር ከተማ ናትና፡፡”