am_tn/mat/05/27.md

2.0 KiB

ማቴዎስ 5፡27-28

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን ለመፈጸም መምጣቱን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ስለዝሙት እና ምኞች ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ሰምታችኋል” በሚለው ሀረግ ውስጥ የሚገኘው “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው፡፡ “አታመንዝር” የሚለው ትዕዛዝ “አንተ” የሚለውን ቃ በውስጡ ይዞዋል ይሁን እንጂ “አንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር መተርጎም ትችላለህ፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-you]] ተመልከት) እንዲህ እንደተባለ ሰምታችኋል ይህ በቀጥታ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) መፈጸም ይህ ቃል አንድን ነገር ማድረግን ያመለክታል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ ይህንን በ MAT 5:22 እንደ ተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ ሴትን ተመልክቶ በልቡ የተመኛት ማንኛውም ሰው አመንዝሯል ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ሴትን ተመልክቶ በልቡ የተመኛት ማንኛውም ሰው ካመነዘረ ሰው እኩሉ ጥፋተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) የተመኛት “እንዲሁም የተመኛት” ወይም “ከእርሷ ጋር ለመተኛት የተመኘ ሰው” በልቡ በዚህ ሥፍራ “ልብ” የሚያመለክተው የአንድን ሰው ሀሳብ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በአእምሮው” ወይም “በሀሳቡ”፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት)