am_tn/luk/23/33.md

1.4 KiB

ሲመጡ

‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው ወታደሮቹን፣ ወንጀለኞቹንና ኢየሱስን ነው፡፡

ሰቀሉት

‹‹የሮም ወታደሮች ኢየሱስን ሰቀሉት››

አንዱን በቀኙ፣ ሌላውን በግራው

‹‹አንዱን ወንጀለኛ በኢየሱስ ቀኝ ሌላውን ወንጀለኛ በኢየሱስ ግራ ጐን ሰቀሉ››

አባት ሆይ፣ ይቅር በላቸው

‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው ኢየሱስን የሰቀሉ ሰዎች ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ አባቱ የጸለየው ለሰቀሉት ሰዎች በመራራት ነበር፡፡

አባት

ይህ ጠቃሚ የእግዚአብሔር መጠሪያ ነው፡፡

የሚያደርጉን አያውቁምና

‹‹ምክንያቱም ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም›› የሮም ወታደሮች የእግዚአብሔርን ልጅ እየሰቀሉ እንደ ነበር አይረዱም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እየሰቀሉ ያለው ማን እንደሆነ በእርግጥ አይረዱም፡፡

ዕጣ ጣሉ

ወታደሮቹ ቁማር በሚመስል አሠራር ተሳተፉ፡፡ ‹‹ቁማር ተጫወቱ››

ዕጣ ጥለው ልብሶቹን ተከፋፈሉ

‹‹እያንዳንዱን የኢየሱስ ልብስ ቁራጭ ማን መውሰድ እንዳለበት ለመወሰን ወታደሮቹ ዕጣ ጣሉ››