# ሲመጡ ‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው ወታደሮቹን፣ ወንጀለኞቹንና ኢየሱስን ነው፡፡ # ሰቀሉት ‹‹የሮም ወታደሮች ኢየሱስን ሰቀሉት›› # አንዱን በቀኙ፣ ሌላውን በግራው ‹‹አንዱን ወንጀለኛ በኢየሱስ ቀኝ ሌላውን ወንጀለኛ በኢየሱስ ግራ ጐን ሰቀሉ›› # አባት ሆይ፣ ይቅር በላቸው ‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው ኢየሱስን የሰቀሉ ሰዎች ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ አባቱ የጸለየው ለሰቀሉት ሰዎች በመራራት ነበር፡፡ # አባት ይህ ጠቃሚ የእግዚአብሔር መጠሪያ ነው፡፡ # የሚያደርጉን አያውቁምና ‹‹ምክንያቱም ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም›› የሮም ወታደሮች የእግዚአብሔርን ልጅ እየሰቀሉ እንደ ነበር አይረዱም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እየሰቀሉ ያለው ማን እንደሆነ በእርግጥ አይረዱም፡፡ # ዕጣ ጣሉ ወታደሮቹ ቁማር በሚመስል አሠራር ተሳተፉ፡፡ ‹‹ቁማር ተጫወቱ›› # ዕጣ ጥለው ልብሶቹን ተከፋፈሉ ‹‹እያንዳንዱን የኢየሱስ ልብስ ቁራጭ ማን መውሰድ እንዳለበት ለመወሰን ወታደሮቹ ዕጣ ጣሉ››