am_tn/luk/06/35.md

1.4 KiB

በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ

“የሰጣችሁት ሰው የሰጣችሁትን ነገር እንዲመልስላችሁ ሳትጠብቁ” ወይም “የሰጣችሁት ሰው ምንም ነገር እንዲመልስላችሁ ሳትጠብቁ”

ሽልማታችሁ ታላቅ ይሆናል

“ታላቅን ሽልማት ትቀበላላችሁ” ወይም “መልካም ክፍያን ታገኛላችሁ” ወይም “ባደረጋችሁት ነገር ምክንያት ጥሩ ስጦታን ታገኛላችሁ”

የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ

“ልጆች” የሚለውን ቃል በቋንቋችሁ ውስጥ የተለመደ የአንድ ሰውን ልጅ ለመግለጽ ጥቅም ላይ በሚውለው ቃል ተርጉሞ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡

የልዑል ልጆች

ልጆች የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ምክንያቱም “የልዑል ልጅ” ከሚለው ከኢየሱስ ማዕረግ ጋር መመሳሰል ስለሌለበት ነው፡፡

ምስጋና ቢስና ክፉ ሰዎች

“እርሱን የማያመሰግኑና ሰዎችና ክፉዎች የሆኑ”

አባታችሁ

ይህ እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ ይህን በቋንቋችሁ ውስጥ ስጋዊ አባትን በሚወክለው ቃል መተርጎም ቢቻል ይመረጣል፡፡