am_tn/luk/06/35.md

24 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ
“የሰጣችሁት ሰው የሰጣችሁትን ነገር እንዲመልስላችሁ ሳትጠብቁ” ወይም “የሰጣችሁት ሰው ምንም ነገር እንዲመልስላችሁ ሳትጠብቁ”
# ሽልማታችሁ ታላቅ ይሆናል
“ታላቅን ሽልማት ትቀበላላችሁ” ወይም “መልካም ክፍያን ታገኛላችሁ” ወይም “ባደረጋችሁት ነገር ምክንያት ጥሩ ስጦታን ታገኛላችሁ”
# የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ
“ልጆች” የሚለውን ቃል በቋንቋችሁ ውስጥ የተለመደ የአንድ ሰውን ልጅ ለመግለጽ ጥቅም ላይ በሚውለው ቃል ተርጉሞ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡
# የልዑል ልጆች
ልጆች የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ምክንያቱም “የልዑል ልጅ” ከሚለው ከኢየሱስ ማዕረግ ጋር መመሳሰል ስለሌለበት ነው፡፡
# ምስጋና ቢስና ክፉ ሰዎች
“እርሱን የማያመሰግኑና ሰዎችና ክፉዎች የሆኑ”
# አባታችሁ
ይህ እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ ይህን በቋንቋችሁ ውስጥ ስጋዊ አባትን በሚወክለው ቃል መተርጎም ቢቻል ይመረጣል፡፡