am_tn/luk/01/76.md

28 lines
2.6 KiB
Markdown

# አዎ፣ አንተ ደግሞ
ዘካርያስ ይህንን ሐረግ ቀጥታ ለልጁ መናገር መጀመሩን ለማሳየት ይጠቀማል፡፡ በራሳችሁ ቋንቋ ይህንን ንግግር ለመጀመር የሚሆን መንገድ መጠቀም ይቻላል፡፡
# አንተ ሕጻን ሆይ ነብይ ትባላለህ
ሰዎች እርሱ ነብይ እንደሆነ ይረዳሉ፡፡ ይህ በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች አንተ ነብይ መሆንህን ያውቃሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
# የበላይ የሆነው
እነዚህ ቃላት እግዚአብሔርን ለመግለጽ የምንጠምባቸው ለስላሴ ዘይቤያዊ ቃላት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የበላይ የሆነውን የሚያገለግል” ወይም “የበላይ ለሆነው ለእግዚአብሔር የሚናገር” (ለስላሴ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
# ከጌታ ፊት ትሄዳለህ
ጌታ ከመምጣቱ በፊት እርሱ ሄዶ ጌታ ወደ እነርሱ እነደሚመጣ ይነግራቸዋል፡፡ ይህንን በሉቃስ 1፡17.
# በጌታ ፊት
የአንድ ሰው “ፊት” የዛን ሰው መገኘት ይወክላል፡፡ ብዙ ጊዜ በትርጉሞች ላይ ተጽፎ አይገኝም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታ” ይህን በሉቃስ 1:17 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡. (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
# መንገዱን ለማዘጋጀት
ይህ ዮሐንስ ሰዎች የጌታን መልዕክት እንዲሰሙና እንዲያምኑ ያዘጋጃቸዋል የሚለውን መልዕክት የያዘ ዘይቤ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
# በኃጢአታቸው ምህረት ማግኘት … የድነትን እውቀት ትሰጣለህ
“እውቀት ትሰጣለህ” የሚለው ሐረግ ማስተማር የሚለውን ትርጉም የያዘ ዘይቤ ነው፡፡ “ድነት” እና “ምህረት” የሚሉት ረቂቅ ቃላት “ማዳን” እና “ይቅር ማለት“ በሚሉት ቃላት ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች በኃጢአታቸው ይቅር መባል መዳናቸውን ያስተምራል” ወይም “ለሰዎች እንዴት እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር በማለት እንዳዳናቸው ያስተምራል” (ምትክ ስም እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)