am_tn/luk/01/76.md

2.6 KiB

አዎ፣ አንተ ደግሞ

ዘካርያስ ይህንን ሐረግ ቀጥታ ለልጁ መናገር መጀመሩን ለማሳየት ይጠቀማል፡፡ በራሳችሁ ቋንቋ ይህንን ንግግር ለመጀመር የሚሆን መንገድ መጠቀም ይቻላል፡፡

አንተ ሕጻን ሆይ ነብይ ትባላለህ

ሰዎች እርሱ ነብይ እንደሆነ ይረዳሉ፡፡ ይህ በአድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች አንተ ነብይ መሆንህን ያውቃሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የበላይ የሆነው

እነዚህ ቃላት እግዚአብሔርን ለመግለጽ የምንጠምባቸው ለስላሴ ዘይቤያዊ ቃላት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የበላይ የሆነውን የሚያገለግል” ወይም “የበላይ ለሆነው ለእግዚአብሔር የሚናገር” (ለስላሴ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጌታ ፊት ትሄዳለህ

ጌታ ከመምጣቱ በፊት እርሱ ሄዶ ጌታ ወደ እነርሱ እነደሚመጣ ይነግራቸዋል፡፡ ይህንን በሉቃስ 1፡17.

በጌታ ፊት

የአንድ ሰው “ፊት” የዛን ሰው መገኘት ይወክላል፡፡ ብዙ ጊዜ በትርጉሞች ላይ ተጽፎ አይገኝም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታ” ይህን በሉቃስ 1:17 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡. (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዱን ለማዘጋጀት

ይህ ዮሐንስ ሰዎች የጌታን መልዕክት እንዲሰሙና እንዲያምኑ ያዘጋጃቸዋል የሚለውን መልዕክት የያዘ ዘይቤ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በኃጢአታቸው ምህረት ማግኘት … የድነትን እውቀት ትሰጣለህ

“እውቀት ትሰጣለህ” የሚለው ሐረግ ማስተማር የሚለውን ትርጉም የያዘ ዘይቤ ነው፡፡ “ድነት” እና “ምህረት” የሚሉት ረቂቅ ቃላት “ማዳን” እና “ይቅር ማለት“ በሚሉት ቃላት ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች በኃጢአታቸው ይቅር መባል መዳናቸውን ያስተምራል” ወይም “ለሰዎች እንዴት እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር በማለት እንዳዳናቸው ያስተምራል” (ምትክ ስም እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)