am_tn/lev/26/34.md

16 lines
1.5 KiB
Markdown

# ከዚያም ምድሪቱ በሰንበት ዓመትዋ ትደሰታለች
ሕዝቡ በየሰባት ዓመቱ ምድሪቱን ባለማረስ የሰንበትን ሕግ መታዘዝ አለባቸው:: እግዚአብሔር ምድሪቱን የሰንበትን ሕግና እረፍት እንደታዘዘ ሰው አድረጐ ይናገራል:: አት: “ከዚያም በሰንበት ሕግ መሠረት ምድሪቱ ታርፋለች” ወይም “ከዚያም የሰንበት ሕግ እንደሚያዝዘው ምድሪቱ አትታረስም” (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)
# ምድሪቱ ታርፋለች
ያልተታረሰውን መሬት እረፍት እንዳገኘ ሰው አድርጐ እግዚአብሔር ይናገራል:: ምድሪቱ መታረስ የለባትም::
# ድንጋጤ እሰድባቸዋለሁ
በእነርሱ ልብ ድንጋጤን መስደድ እነርሱን ማሳፈርን ይወክላል:: አት: “እጅግ እንዲታፍሩ አደርጋችኋለሁ”:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
# ከሰይፍ እንደሚትሸሹ
ሰይፍ የሚወክለው ሰይፍን በመያዝ ሊገድል የተዘጋጀ ሰው ወይም ከጠላት ሠራዊት የሚሆን ውጊያን ነው:: አት: “በሰይፍ ከሚያሳድዳችሁ እንደሚትሸሹ” ወይም “ከጠላት ሠራዊት እንደሚትሸሹ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)