# ከዚያም ምድሪቱ በሰንበት ዓመትዋ ትደሰታለች ሕዝቡ በየሰባት ዓመቱ ምድሪቱን ባለማረስ የሰንበትን ሕግ መታዘዝ አለባቸው:: እግዚአብሔር ምድሪቱን የሰንበትን ሕግና እረፍት እንደታዘዘ ሰው አድረጐ ይናገራል:: አት: “ከዚያም በሰንበት ሕግ መሠረት ምድሪቱ ታርፋለች” ወይም “ከዚያም የሰንበት ሕግ እንደሚያዝዘው ምድሪቱ አትታረስም” (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ) # ምድሪቱ ታርፋለች ያልተታረሰውን መሬት እረፍት እንዳገኘ ሰው አድርጐ እግዚአብሔር ይናገራል:: ምድሪቱ መታረስ የለባትም:: # ድንጋጤ እሰድባቸዋለሁ በእነርሱ ልብ ድንጋጤን መስደድ እነርሱን ማሳፈርን ይወክላል:: አት: “እጅግ እንዲታፍሩ አደርጋችኋለሁ”:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ) # ከሰይፍ እንደሚትሸሹ ሰይፍ የሚወክለው ሰይፍን በመያዝ ሊገድል የተዘጋጀ ሰው ወይም ከጠላት ሠራዊት የሚሆን ውጊያን ነው:: አት: “በሰይፍ ከሚያሳድዳችሁ እንደሚትሸሹ” ወይም “ከጠላት ሠራዊት እንደሚትሸሹ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)