1.4 KiB
1.4 KiB
በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ
ይህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኝ የመሥዋዕት መሠዊያ ነው
ለመሠዊያው ያስተሠርይለት
እንደ ቅዱስ ቦታና መገናኛ ድንኳን መሠዊያው ከሰዎች ኃጢአት የተነሣ ርኩስ ይሆናል
የመሠዊያው ቀንዶች
በመሠዊያው ማዕዘናት ያሉ ቅርጾች ይህም የመሠዊያው ማዕዘናት ያመለክታል:: እንደ በሬ ቀንዶች የተቀረጹ ናቸው:: በዘሌዋዊያን 4:7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ለማንጻት
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች መጠቀሚያ የሚገባው መሠዊያ ንጹህ እንደሆነ ተገልጾአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔርም ይለዩት ከእስራኤልም ሕዝብ ርኩስ ተግባራት ያርቁት
ለእግዚአብሔር የተለየው መሠዊያ ከሕዝቡም ኃጢአት አንደተለየ ተደርጐ ተነግሮአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ርኩስ ድርጊቶች
በእግዚአብሔር ፊት ሰዎች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚያደርጉ ኃጢአታዊ ድርጊቶች ርኩስ ድርጊቶች ተብለው ተነግረዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)