am_tn/lam/05/01.md

1.9 KiB

አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ

“አስብ” የሚለው ዘይቤአዊ አገላለፅ ነው። “አቤቱ፥ የሆነብንን አስታውስ”

ተመልከት ስድባችንንም እይ

“ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም”

ርስታችን ለመጻተኞች፣ ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ

በቀጠተኛ አገላለፅም ሊቀመጥ የሚችል ዓረፍተ ነገር ነው። “ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች አሳልፈህ ሰጠህ” ወይንም “ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ታልፈው እንዲሰጡ ፈቀድክ።

ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን ፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ

የእየሩሳሌም ሰዎች ለጠብቃቸው የሚችል ማንም የለም፤ ምክንያቱም ወንዶች ልጆቻቸው ወይ በጦርነት ላይ ሞተዋል አልያም ደግሞ በምርኮ ተወስደዋል። ይህ ደግሞ የሚያመላክተው በእስራኤል የቀሩት ወላጅ አልባዎች እና መበለቶች መሆናቸውን ነው።

ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው

እነኚህ ቃላት አንድ አይነት ትርጉም ሲኖራቸው፤ አባት የሌላቸው ሰዎችን ያመላክታል

ውኃችንን በብር ጠጣን እንጨታችንን በዋጋ ገዛን

ይህ የሚያሳየው በአንድ ግዜ በነፃ ይጠቀሙ የነበሩትን ውሃ እና እንጨት ጠላቶቻቸው እያስከፈሏቸው እንደሆነ ነው። “የራሳችን የሆነውን ውሃ ለመጠጣት እና የራሳችንን እንጨት ለመጠቀም መክፈል አለብን”

እንጨታችንን በዋጋ ገዛን

ይሄ በቀጥታ መልኩ ሊገለፅ ይችላል። “ጠላቶታችን የገዛ እንጨታችንን ይሸጡልናል”