1.3 KiB
1.3 KiB
አጠቃላይ መረጃ፡-
ኤርምያስ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጥሏል፡፡
ስለ ስምህ ብለህ
እዚህ ላይ የእግዚአብሔር “ስም” መልካም ማንነቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ መልካም ማንነትህ ብለህ” ወይም “ማንኛውም ሰው አንተ በጣም ታላቅና ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ እንደሆንህ ማየት ይችል ዘንድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
የክብርህ ዙፋን
የእግዚአብሔር “ዙፋን” በጽዮን ማለትም በኢየሩሳሌም ተወክሏል፡፡ በተጨማሪ የእርሱ “ዙፋን” እርሱ እንደ ንጉስ የሚገዛበትን ስፍራ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአንተ የክብር ዙፋን የሚገኝባትን ጽዮንን ታዋርዳታለህን” ወይም “አንተ እንደ ንጉስ ተቀምጠህ የምትገዛባትን ጽዮንን አታዋርዳት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ሰማያት በራሳቸው ዝናብ ማፍሰስ ይችላሉን
“ሰማያት ዝናብ መቼ ማፍሰስ እንዳለባቸው በራሳቸው መወሰን ይችላሉን?”