# አጠቃላይ መረጃ፡- ኤርምያስ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጥሏል፡፡ # ስለ ስምህ ብለህ እዚህ ላይ የእግዚአብሔር “ስም” መልካም ማንነቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ መልካም ማንነትህ ብለህ” ወይም “ማንኛውም ሰው አንተ በጣም ታላቅና ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ እንደሆንህ ማየት ይችል ዘንድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ) # የክብርህ ዙፋን የእግዚአብሔር “ዙፋን” በጽዮን ማለትም በኢየሩሳሌም ተወክሏል፡፡ በተጨማሪ የእርሱ “ዙፋን” እርሱ እንደ ንጉስ የሚገዛበትን ስፍራ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአንተ የክብር ዙፋን የሚገኝባትን ጽዮንን ታዋርዳታለህን” ወይም “አንተ እንደ ንጉስ ተቀምጠህ የምትገዛባትን ጽዮንን አታዋርዳት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ) # ሰማያት በራሳቸው ዝናብ ማፍሰስ ይችላሉን “ሰማያት ዝናብ መቼ ማፍሰስ እንዳለባቸው በራሳቸው መወሰን ይችላሉን?”