am_tn/isa/14/21.md

4.0 KiB

ልጆቹ የሚታረዱበትን ቦታ አዘጋጅ

‹‹የሚታረዱበት›› የሚለውን፣ ‹‹የሚገደሉበት›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የባቢሎንን ንጉሥ ልጆች ለመግደል ተዘጋጁ››

ለአባቶቻቸው ርኩሰት

‹‹ርኩሰት›› የሚለውን፣ ‹‹ታላቅ ኀጢአት›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቶቻቸው ለመፈጸሙት ታላቅ ኀጢአት››

ከእንግዲህ አይነሡም

‹‹መነሣት›› ኀያል መሆንን ወይም ማጥቃትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ኀያል እንዳይሆኑ›› ወይም፣ ‹‹ከእንግዲህ እንዳያጠቁ››

ምድርን እንዲወርሱ

ይህ የሚያመለክተው የምድር ሰዎችን መቆጣጠርን ሲሆን፣ እዚህ ላይ ግን እነርሱን ድል ማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምድር ሰዎችን መቆጣጠር›› ወይም፣ ‹‹የምድርን ሕዝብ ድል ማድረግ››

ዓለምን በከተሞች በሙላት

ይህ ዓለም ብዙ ከተሞች እንዲኖሩዋት ማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመላው ዓለም ከተሞች መሥራት››

በእነርሱ ላይ እነሣለሁ

ይህ ማለት እግዚአብሔር እነርሱ ላይ አንዳች ነገር ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው የባቢሎንን ሕዝብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አጠቃቸዋለሁ›› ወይም፣ ‹‹የሚያጠቋቸው ሰዎች እልካለሁ››

የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

ያህዌ ስሙን በመጥራት የተናገረው እርግጥ መሆኑን ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰራዊት ጌታ ያህዌ የሚለው እንዲህ ነው›› ወይም፣ ‹‹እኔ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ያልሁት እንዲህ ነው››

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደተረጐምኸው ተመልከት፡፡

የባቢሎንን ስም፣ ትውልድና ትሩፋኖችዋን እቆርጣለሁ

‹‹እቆርጣለሁ›› አጠፋለሁ ማለት ነው፡፡ ‹‹ባቢሎን›› የባቢሎንን ሕዝብ ይወክላል፡፡ እንዲሁም፣ ‹‹ስም›› የባቢሎንን ዝና ወይም፣ እንደ መንግሥት ባቢሎን ራሷን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሕዝቡ ልጆችና የልጅ ልጆች ጋር ባቢሎንን አጠፋለሁ››

አደርጋታለሁ

‹‹እርሷ›› የባቢሎንን ከተማ ያመለክታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ከተሞች በሴቶች ስም ይጠራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲህም… አደርጋታለሁ››

የጃርት መኖሪያ

ይህ የሚያመለክተው የሚኖርባቸው ስለማይኖር አራዊት በከተማው ውስጥ እንደሚኖሩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጃርቶች የሚኖሩበት ቦታ›› ወይም፣ ‹‹የዱር አራዊት የሚኖሩበት ቦታ››

ረግረግ ቦታ

የታቆረና የተከማቸ ውሃ እንዳኖርበት ማድረግ ከተማው የእነዚህ ነገሮች መኖሪያ እንዲሆን ማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የታቆረ ውሃ መኖሪያ ቦታ››

በጥፋት መጥረጊያ እጠርጋታለሁ

ይህ የሚያመለክተው የባቢሎንን ጨርሶ መውደምና ሰዎች ጠርገው የሚጥሉት ቆሻሻ ይመስል፣ ከእንግዲህ እንደማትኖር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመጥረጊያ እንደሚጠረግ ነገር ጨርሶ አጠፋታለሁ››