52 lines
4.0 KiB
Markdown
52 lines
4.0 KiB
Markdown
|
# ልጆቹ የሚታረዱበትን ቦታ አዘጋጅ
|
||
|
|
||
|
‹‹የሚታረዱበት›› የሚለውን፣ ‹‹የሚገደሉበት›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የባቢሎንን ንጉሥ ልጆች ለመግደል ተዘጋጁ››
|
||
|
|
||
|
# ለአባቶቻቸው ርኩሰት
|
||
|
|
||
|
‹‹ርኩሰት›› የሚለውን፣ ‹‹ታላቅ ኀጢአት›› ማለት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቶቻቸው ለመፈጸሙት ታላቅ ኀጢአት››
|
||
|
|
||
|
# ከእንግዲህ አይነሡም
|
||
|
|
||
|
‹‹መነሣት›› ኀያል መሆንን ወይም ማጥቃትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ኀያል እንዳይሆኑ›› ወይም፣ ‹‹ከእንግዲህ እንዳያጠቁ››
|
||
|
|
||
|
# ምድርን እንዲወርሱ
|
||
|
|
||
|
ይህ የሚያመለክተው የምድር ሰዎችን መቆጣጠርን ሲሆን፣ እዚህ ላይ ግን እነርሱን ድል ማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምድር ሰዎችን መቆጣጠር›› ወይም፣ ‹‹የምድርን ሕዝብ ድል ማድረግ››
|
||
|
|
||
|
# ዓለምን በከተሞች በሙላት
|
||
|
|
||
|
ይህ ዓለም ብዙ ከተሞች እንዲኖሩዋት ማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመላው ዓለም ከተሞች መሥራት››
|
||
|
|
||
|
# በእነርሱ ላይ እነሣለሁ
|
||
|
|
||
|
ይህ ማለት እግዚአብሔር እነርሱ ላይ አንዳች ነገር ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ‹‹እነርሱ›› የሚያመለክተው የባቢሎንን ሕዝብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አጠቃቸዋለሁ›› ወይም፣ ‹‹የሚያጠቋቸው ሰዎች እልካለሁ››
|
||
|
|
||
|
# የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል
|
||
|
|
||
|
ያህዌ ስሙን በመጥራት የተናገረው እርግጥ መሆኑን ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰራዊት ጌታ ያህዌ የሚለው እንዲህ ነው›› ወይም፣ ‹‹እኔ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ያልሁት እንዲህ ነው››
|
||
|
|
||
|
# የሰራዊት ጌታ ያህዌ
|
||
|
|
||
|
ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደተረጐምኸው ተመልከት፡፡
|
||
|
|
||
|
# የባቢሎንን ስም፣ ትውልድና ትሩፋኖችዋን እቆርጣለሁ
|
||
|
|
||
|
‹‹እቆርጣለሁ›› አጠፋለሁ ማለት ነው፡፡ ‹‹ባቢሎን›› የባቢሎንን ሕዝብ ይወክላል፡፡ እንዲሁም፣ ‹‹ስም›› የባቢሎንን ዝና ወይም፣ እንደ መንግሥት ባቢሎን ራሷን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከሕዝቡ ልጆችና የልጅ ልጆች ጋር ባቢሎንን አጠፋለሁ››
|
||
|
|
||
|
# አደርጋታለሁ
|
||
|
|
||
|
‹‹እርሷ›› የባቢሎንን ከተማ ያመለክታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ከተሞች በሴቶች ስም ይጠራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲህም… አደርጋታለሁ››
|
||
|
|
||
|
# የጃርት መኖሪያ
|
||
|
|
||
|
ይህ የሚያመለክተው የሚኖርባቸው ስለማይኖር አራዊት በከተማው ውስጥ እንደሚኖሩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጃርቶች የሚኖሩበት ቦታ›› ወይም፣ ‹‹የዱር አራዊት የሚኖሩበት ቦታ››
|
||
|
|
||
|
# ረግረግ ቦታ
|
||
|
|
||
|
የታቆረና የተከማቸ ውሃ እንዳኖርበት ማድረግ ከተማው የእነዚህ ነገሮች መኖሪያ እንዲሆን ማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የታቆረ ውሃ መኖሪያ ቦታ››
|
||
|
|
||
|
# በጥፋት መጥረጊያ እጠርጋታለሁ
|
||
|
|
||
|
ይህ የሚያመለክተው የባቢሎንን ጨርሶ መውደምና ሰዎች ጠርገው የሚጥሉት ቆሻሻ ይመስል፣ ከእንግዲህ እንደማትኖር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በመጥረጊያ እንደሚጠረግ ነገር ጨርሶ አጠፋታለሁ››
|