am_tn/hos/13/16.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

በአምላኳ ላይ አምጻለችና ሰማሪያ ኀጢአተኛ ትሆናለች

እዚህ ስፍራ "ሰማርያ" የሚለው በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ ሀጢአተኛ የሆኑትን በከተማይቱ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ይወድቃሉ

እዚህ ስፍራ "ይወድቃሉ" የሚለው መሞትን ይወከወላል፡፡ (ዩፊምዝም/የማያስድትን ቃለ ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚለው የሚወክለው በጦርነት ጊዜ ሰይፍ የሚይዙ የጠላት ወታደሮችን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ትንንሽ ልጆቻቸው ተደፍጥጠው ቁርጥራጭ ይደረጋሉ፣ ነብሰጡር ሴቶቻቸው በገሃድ ይደፈራሉ

እነዚህ ሀረጋት በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "ጠላት ትንንሽ ልጆቻቸውን ደፍጥጠው ይቆራርጣሉ፣ ነብሰ ጡር ሴቶችን በገሃድ ይደፍራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)