3.2 KiB
ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይም በመን እንነጻለን?
ሶስቱም ጥያቄዎች ሁሉ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: የተደረገውን ለመግለጽ የሚናገሩት ምንም እንደሌለ ትኩረት ለመስጠት እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማሉ፡፡ አት “ጌታዬ የምንናገረው የለንም የሚረባ ነገር መናገር አንችልም ራሳችንን ንጹህ ማድረግ አንችልም” (ተመሣሣይ ተጓዳኝ አገላለጽ እና ሽንገላ አዘል ጥያቄዎች ይመልከቱ)
ለጌታዬ ምን እንላለን …. የጌታዬ ባሪያዎች
እዚህ ጌታዬ ዮሴፍን ያመለክታል ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው በሁለተኛ ወገን ሰው መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ምን አንላለን … ባሪያዎችህ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የአገልጋዮችን/የባሪያችህን በደል ገልጦአል
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች ያቀርባሉ :: እዚህ ገለጠ የሚለው እግዚአብሔር ወንድሞቹ ያደረጉትን ገለጠ ማለት አይደለም:: ነገር ግን እነርሱ ስላደረጉት ነገር እግዚአብሔር እየቀጣቸው ነው የሚል ትርጉም አለው:: አት “እግዚአብሔር ላለፈው ኃጢአት እየቀጣቸው ነው”
የባሪያዎችህን በደል
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች ያቀርባሉ:; ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: በአንደኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “በደላችንን” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እንግዲህ ጽዋው በእጁ የተገኘበት
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰው ይወክላል:: እንዲሁም የተገኘበት የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:; አት “ጽዋህን የወሰደው” (ምትክ ቃል አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህን ማድረግ ከእኔ ይራቅ
አንድ ሰው የማያደርገው አንድ ነገር ያ ሰው ከራሱ አርቆ የሚያቀምጠው ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ያን ነገር የሚያደርግ የእኔ ዓይነት አይደለም” (ዘይቤያዊ አነጋYገር ይመልከቱ)
ጽዋው በእጁ የተገኘበት ሰው
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰው ይወክላል:: እንዲሁም የተገኘበት የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:; አት “ጽዋዬን የወሰደው ሰው” (ምትክ ቃል አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)