am_tn/gen/44/16.md

28 lines
3.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይም በመን እንነጻለን?
ሶስቱም ጥያቄዎች ሁሉ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: የተደረገውን ለመግለጽ የሚናገሩት ምንም እንደሌለ ትኩረት ለመስጠት እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማሉ፡፡ አት “ጌታዬ የምንናገረው የለንም የሚረባ ነገር መናገር አንችልም ራሳችንን ንጹህ ማድረግ አንችልም” (ተመሣሣይ ተጓዳኝ አገላለጽ እና ሽንገላ አዘል ጥያቄዎች ይመልከቱ)
# ለጌታዬ ምን እንላለን …. የጌታዬ ባሪያዎች
እዚህ ጌታዬ ዮሴፍን ያመለክታል ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው በሁለተኛ ወገን ሰው መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ምን አንላለን … ባሪያዎችህ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
# እግዚአብሔር የአገልጋዮችን/የባሪያችህን በደል ገልጦአል
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች ያቀርባሉ :: እዚህ ገለጠ የሚለው እግዚአብሔር ወንድሞቹ ያደረጉትን ገለጠ ማለት አይደለም:: ነገር ግን እነርሱ ስላደረጉት ነገር እግዚአብሔር እየቀጣቸው ነው የሚል ትርጉም አለው:: አት “እግዚአብሔር ላለፈው ኃጢአት እየቀጣቸው ነው”
# የባሪያዎችህን በደል
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች ያቀርባሉ:; ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: በአንደኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “በደላችንን” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
# እንግዲህ ጽዋው በእጁ የተገኘበት
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰው ይወክላል:: እንዲሁም የተገኘበት የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:; አት “ጽዋህን የወሰደው” (ምትክ ቃል አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
# ይህን ማድረግ ከእኔ ይራቅ
አንድ ሰው የማያደርገው አንድ ነገር ያ ሰው ከራሱ አርቆ የሚያቀምጠው ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ያን ነገር የሚያደርግ የእኔ ዓይነት አይደለም” (ዘይቤያዊ አነጋYገር ይመልከቱ)
# ጽዋው በእጁ የተገኘበት ሰው
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰው ይወክላል:: እንዲሁም የተገኘበት የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:; አት “ጽዋዬን የወሰደው ሰው” (ምትክ ቃል አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)