am_tn/gen/27/36.md

1.8 KiB

ያዕቆብ መባሉ የሚታወቅ አይደለምን?

ዔሣው በያዕቆብ ላይ ያለውን ቁጣ ለመጨመር ጥያቄ ይጠቀማል:: አት ያዕቆብ በእርግጥ ለወንድሜ ትክክለኛ ስም ነው:: (ቅኔያዊ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)

ያዕቆብ

ተርጓሚዎች እንዲህ የሚለውን የግርጌ ማስታወሻ ይጠቀማሉ ያዕቆብ የሚለው ስም ተረከዙን ያዘ የሚል ትርጉም አለው በመሠረታዊው ቋንቋ ቃሉ አታላይ የሚል አንድምታ አለው::

ብኩርናዬን ወሰደብኝ

ይህ ብኩርና እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚወሰድ አድርጐ ይናገራል:: አት: “የእኔ የሆነው ብኩርና በማታለሉ ምክንያት የእርሱ ሆኖአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::

አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ

ይህ ምርቃት እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚቀማ አድርጐ ይናገራል:: አት : “አታልሎህ በእኔ ፈንታ እርሱን እንዲትመርቅ አድረጐሃል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::

ለእኔ ያስቀረኼው ምንም ምርቃት የለም?

ያዕቆብን የባረከውን ዓይነት በረከት አባቱ እንደማይባርከው ዔሣው ያውቃል ይስሐቅ ያዕቆብን በሚባርክበት ጊዜ ሳይናገር የቀረው ካለ ዔሣው ይጠይቀዋል

ልጄ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?

ይስሐቅ ጥያቄ በመጠቀም ምንም ሊያደርገው የሚችለው ነገር እንደሌለ በአጽንዖት ይናገራል:: አት “ለአንተ የማደርገው የቀረ ነገር የለም” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)