# ያዕቆብ መባሉ የሚታወቅ አይደለምን? ዔሣው በያዕቆብ ላይ ያለውን ቁጣ ለመጨመር ጥያቄ ይጠቀማል:: አት ያዕቆብ በእርግጥ ለወንድሜ ትክክለኛ ስም ነው:: (ቅኔያዊ ጥያቄዎችን ይመልከቱ) # ያዕቆብ ተርጓሚዎች እንዲህ የሚለውን የግርጌ ማስታወሻ ይጠቀማሉ ያዕቆብ የሚለው ስም ተረከዙን ያዘ የሚል ትርጉም አለው በመሠረታዊው ቋንቋ ቃሉ አታላይ የሚል አንድምታ አለው:: # ብኩርናዬን ወሰደብኝ ይህ ብኩርና እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚወሰድ አድርጐ ይናገራል:: አት: “የእኔ የሆነው ብኩርና በማታለሉ ምክንያት የእርሱ ሆኖአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ):: # አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ ይህ ምርቃት እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚቀማ አድርጐ ይናገራል:: አት : “አታልሎህ በእኔ ፈንታ እርሱን እንዲትመርቅ አድረጐሃል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ):: # ለእኔ ያስቀረኼው ምንም ምርቃት የለም? ያዕቆብን የባረከውን ዓይነት በረከት አባቱ እንደማይባርከው ዔሣው ያውቃል ይስሐቅ ያዕቆብን በሚባርክበት ጊዜ ሳይናገር የቀረው ካለ ዔሣው ይጠይቀዋል # ልጄ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ይስሐቅ ጥያቄ በመጠቀም ምንም ሊያደርገው የሚችለው ነገር እንደሌለ በአጽንዖት ይናገራል:: አት “ለአንተ የማደርገው የቀረ ነገር የለም” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)