am_tn/ezk/27/19.md

2.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

"አንቺ" እና "የአንቺ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ጢሮስን ነው፡፡

ዳን..ያዋን…ኦሴል..ድዳን..ዐረብ.. ቄዳር

እነዚህ የቦታዎች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ዳን እና ያዋን

ይህ ለዳን እና ያዋን ነዋሪዎች ሜቶናሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "የዳን እና ያዋን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የሚቀጠቀጥ/የሚጠፈጠፍ ብረት

በመዶሻ ቅርጽ ሊይዝ የሚችል የብረት አይነት

ቀረፋ

ከዛፍ ቅርፊት የሚገኝ የቅመም አይነት፡፡ "ብርጉድ" የዚህ አይነቱ ቅመም ሌላ ስም ነው፡፡ (በእርግጠኝነት የማይታወቁትን ነገሮች መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ጠጅ ሳር

እንደ ሽቶ የሚያገለግል እና ሰዎች ለመድሀኒትነት የሚጠቀሙበት የሳር አይነት

ደዳን …ነበረች

ይህ ለድን ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "የድዳን ሰዎች … ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የኮርቻ ጨርቅ/ምንጣፍ

የኮርቻ ምንጣፍ በፈረስ ወይም ከኮርቻ ስር የሚደረግ ለመቀመጫነት የሚውል ቁራጭ ጨርቅ ነው፡፡

አረብ

ለአረብ ሰዎች የሚውል ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ ነው፡፡ "የአረብ አገር ሰዎች" ወይም "አረቦች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)