# አያያዥ ሀሳብ፡ ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ ጢሮስ መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ # አጠቃላይ መረጃ፡ "አንቺ" እና "የአንቺ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ጢሮስን ነው፡፡ # ዳን..ያዋን…ኦሴል..ድዳን..ዐረብ.. ቄዳር እነዚህ የቦታዎች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ) # ዳን እና ያዋን ይህ ለዳን እና ያዋን ነዋሪዎች ሜቶናሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "የዳን እና ያዋን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # የሚቀጠቀጥ/የሚጠፈጠፍ ብረት በመዶሻ ቅርጽ ሊይዝ የሚችል የብረት አይነት # ቀረፋ ከዛፍ ቅርፊት የሚገኝ የቅመም አይነት፡፡ "ብርጉድ" የዚህ አይነቱ ቅመም ሌላ ስም ነው፡፡ (በእርግጠኝነት የማይታወቁትን ነገሮች መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ) # ጠጅ ሳር እንደ ሽቶ የሚያገለግል እና ሰዎች ለመድሀኒትነት የሚጠቀሙበት የሳር አይነት # ደዳን …ነበረች ይህ ለድን ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "የድዳን ሰዎች … ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # የኮርቻ ጨርቅ/ምንጣፍ የኮርቻ ምንጣፍ በፈረስ ወይም ከኮርቻ ስር የሚደረግ ለመቀመጫነት የሚውል ቁራጭ ጨርቅ ነው፡፡ # አረብ ለአረብ ሰዎች የሚውል ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ ነው፡፡ "የአረብ አገር ሰዎች" ወይም "አረቦች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)