am_tn/exo/01/13.md

16 lines
996 B
Markdown

# • በመከራ ገዙአቸው
ጭካኔ በተሞላበትና ርህራሄ በለሌው ስሜት ግፍ ይፈጽሙባቸው ነበር።
# • ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር
የአንድ ዛፍ ፍሬ መራራ ከሆነ እንደማይበላና ደስ እንደማይል ሁሉ የእስራኤላውያን ህይወት እለት ተዕለት በሚደርስባቸው ጭካነ መራራ በመሆኑ ደስተኞች አልነበሩም ማለት ነው። አባባሉ በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው።
# • በጡብ ሥራ
ለቤት ሥራ የሚውል ከጭቃና ከሸክላ አፈር እንዲሁም በዘመናዊ መንገድ ከሲሚንቶ የሚሰራ ብሎኬት መሳይ ነገር ማለት ነው
# • በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ
ግብጻውያን እስራኤላውያንን የተለያዩና በጣም ከባድ የሆነ የጉልበት ሥራዎችን ያሰሩአቸው ነበር።