# • በመከራ ገዙአቸው ጭካኔ በተሞላበትና ርህራሄ በለሌው ስሜት ግፍ ይፈጽሙባቸው ነበር። # • ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር የአንድ ዛፍ ፍሬ መራራ ከሆነ እንደማይበላና ደስ እንደማይል ሁሉ የእስራኤላውያን ህይወት እለት ተዕለት በሚደርስባቸው ጭካነ መራራ በመሆኑ ደስተኞች አልነበሩም ማለት ነው። አባባሉ በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው። # • በጡብ ሥራ ለቤት ሥራ የሚውል ከጭቃና ከሸክላ አፈር እንዲሁም በዘመናዊ መንገድ ከሲሚንቶ የሚሰራ ብሎኬት መሳይ ነገር ማለት ነው # • በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ ግብጻውያን እስራኤላውያንን የተለያዩና በጣም ከባድ የሆነ የጉልበት ሥራዎችን ያሰሩአቸው ነበር።