am_tn/deu/28/01.md

1.3 KiB

ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ድምፅ

እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እርሱ የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ለሚናገረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ትጠብቀው ዘንድ

“ትታዘዘው ዘንድ”

ከላይ ያደርግሃል

ሙሴ ከፍ ባለ ኮረብታ ላይ በአካል ከፍ እንደ ማለት አስፈላጊ ስለ መሆን ወይም ታላቅ ስለ መሆን ይናገራል። አ.ት፡ “ከ -- ይልቅ በጣም አስፈላጊ ያደርግሃል” ወይም “ከ-- ይልቅ ታላቅ ያደርግሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡብሃል፣ ይደርሱብሃልም

ሙሴ በረከቶችን የሚገልጻቸው በድንገት እንደሚያጠቃቸው ወይም አሳዶ እንደሚይዛቸው ሰው አድርጎ ነው። አ.ት፡ “ፈጽሞ በምትገረምበት እንዲህ ባለ መንገድ እግዚአብሔር ይባርክሃል፣ ይኸውም ልታመልጥ በማትችልበት መልኩ ይባርክሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)