16 lines
1.3 KiB
Markdown
16 lines
1.3 KiB
Markdown
|
# ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ድምፅ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እርሱ የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ለሚናገረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# ትጠብቀው ዘንድ
|
||
|
|
||
|
“ትታዘዘው ዘንድ”
|
||
|
|
||
|
# ከላይ ያደርግሃል
|
||
|
|
||
|
ሙሴ ከፍ ባለ ኮረብታ ላይ በአካል ከፍ እንደ ማለት አስፈላጊ ስለ መሆን ወይም ታላቅ ስለ መሆን ይናገራል። አ.ት፡ “ከ -- ይልቅ በጣም አስፈላጊ ያደርግሃል” ወይም “ከ-- ይልቅ ታላቅ ያደርግሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# እነዚህ በረከቶች ሁሉ ይመጡብሃል፣ ይደርሱብሃልም
|
||
|
|
||
|
ሙሴ በረከቶችን የሚገልጻቸው በድንገት እንደሚያጠቃቸው ወይም አሳዶ እንደሚይዛቸው ሰው አድርጎ ነው። አ.ት፡ “ፈጽሞ በምትገረምበት እንዲህ ባለ መንገድ እግዚአብሔር ይባርክሃል፣ ይኸውም ልታመልጥ በማትችልበት መልኩ ይባርክሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
|