am_tn/amo/04/08.md

2.0 KiB

ሁለት ወይም ሶስት የተጎዱ ከተማዎች

እዚህ ላይ “ከተማዎች” የሚለው ቃል የሚመለክተው የዚያ ከተማ ነዋሪዎችን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የሁለት ወይም የሶስት ከተማ ሕዝቦች ተንገዳገዱ፡፡”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

በዋግውና በአረማሞ መታኋችሁ

እዚሀ ላይ “መታኋችሁ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰብላቸውን መውደም ነው፡፡”የአሞፅ ትርጉም “እህላችሁን በዋግና በአረማሞ መታሁባችሁ”ወይም“እህላችሁን በዋግና በአረማሞ ደመሰስኩት”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ዋግ

ይሄ ዕፅዋትን የሚደርቅና የሚገድል ነገር ነው፡፡

ወደ እኔ አልተመለሳችሁም

“ወደ እግዚአብሔር መመለስ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራስን ለእግዚአብሔር ፈፅሞ እንደገና ማስገዛትን ነው፡፡ይሄንን በአሞፅ 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“ራሳችሁን እንደገና ፈፅሞ አላስገዛችሁልኝም፡፡” (ምሣሌያዊ አነጋገርን ይመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለመግለፅ እግዚአብሔር በራሱ ሥም ይናገራል፡፡እነዚህን ቃላት በአሞፅ 2፤11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህንን ነው”ወይም “ይህንን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ”(መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካል)