am_tn/act/13/16.md

2.0 KiB

የሐዋርያት ሥራ 13፡ 16-18

አጠቃላይ መረጃ: ጳውሎስ በአንጾኪያ ጲስድያ ውስጥ በሚገኘው ምኩራብ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች መናገር ጀመረ፡፡ ንግግሩን የጀመረው በእስራኤል ታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ ነገሮችን በማንሳት ነው፡፡ በእጆቹ እያሳየ ይህ ለመናገር ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት እጆቹን ማንቀሳቀሱ ልሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “ለመናገር እየተዘጋጀ መሆኑን ለማሳየት እጆችን ወደላይ ዘረጋቸው፡፡” እናንተ እግዚአብሔርን የሚትፈሩ ሰዎች ሆይ ይህ ወደ ክርስትና የተለወጡ አሕዛብን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “እናንተ ከእስራኤል ወገን ያልሆናችሁ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚታመልኩ ሰዎች ሆይ፡፡” አድምጡ "እኔን አድምጡ" ወይም "አሁን ልናገር ያለሁትን ነገር አድምጡ" የእነዚህ የእስራኤል ሕዝቦች አምላክ "የእስራኤል ሕዝብ የሚያመልከው እግዚአብሔር" አባቶቻችንን መረጠ በዚህ ሥፍራ ጥቅም ላይ የዋለው “እኛ” የሚለው ቃል ሁሉን የማያካትት ሆኖ ጳውሎስን እና የእርሱ ወገን የሆኑትን አይሁዳዊያንን የሚያካትት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ከብዙ ዘመናት በፊት የአይሁድ ሕዝብን መረጠ፡፡” (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-exclusive) እነርሱ በዚያ በቆዩ ጊዜ "እስራኤላዊያን በዚያ በቆዩ ጊዜ" ከዚያ እየመራ አወጣቸው "እግዚአብሔር እስራኤላዊያን ከግብጽ ምድር እየመራ አወጣቸው" ታገሳቸው "እግዚአብሔር እነርሱ ታገሰ" ወይም "እግዚአብሔር አለመታዘዛቸው ታገሰ"