21 lines
2.0 KiB
Markdown
21 lines
2.0 KiB
Markdown
|
# የሐዋርያት ሥራ 13፡ 16-18
|
||
|
|
||
|
አጠቃላይ መረጃ:
|
||
|
ጳውሎስ በአንጾኪያ ጲስድያ ውስጥ በሚገኘው ምኩራብ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች መናገር ጀመረ፡፡ ንግግሩን የጀመረው በእስራኤል ታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ ነገሮችን በማንሳት ነው፡፡
|
||
|
በእጆቹ እያሳየ
|
||
|
ይህ ለመናገር ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት እጆቹን ማንቀሳቀሱ ልሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “ለመናገር እየተዘጋጀ መሆኑን ለማሳየት እጆችን ወደላይ ዘረጋቸው፡፡”
|
||
|
እናንተ እግዚአብሔርን የሚትፈሩ ሰዎች ሆይ
|
||
|
ይህ ወደ ክርስትና የተለወጡ አሕዛብን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “እናንተ ከእስራኤል ወገን ያልሆናችሁ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚታመልኩ ሰዎች ሆይ፡፡”
|
||
|
አድምጡ
|
||
|
"እኔን አድምጡ" ወይም "አሁን ልናገር ያለሁትን ነገር አድምጡ"
|
||
|
የእነዚህ የእስራኤል ሕዝቦች አምላክ
|
||
|
"የእስራኤል ሕዝብ የሚያመልከው እግዚአብሔር"
|
||
|
አባቶቻችንን መረጠ
|
||
|
በዚህ ሥፍራ ጥቅም ላይ የዋለው “እኛ” የሚለው ቃል ሁሉን የማያካትት ሆኖ ጳውሎስን እና የእርሱ ወገን የሆኑትን አይሁዳዊያንን የሚያካትት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ከብዙ ዘመናት በፊት የአይሁድ ሕዝብን መረጠ፡፡” (ተመልከት: [[rc://*/ta/man/translate/figs-exclusive]])
|
||
|
እነርሱ በዚያ በቆዩ ጊዜ
|
||
|
"እስራኤላዊያን በዚያ በቆዩ ጊዜ"
|
||
|
ከዚያ እየመራ አወጣቸው
|
||
|
"እግዚአብሔር እስራኤላዊያን ከግብጽ ምድር እየመራ አወጣቸው"
|
||
|
ታገሳቸው
|
||
|
"እግዚአብሔር እነርሱ ታገሰ" ወይም "እግዚአብሔር አለመታዘዛቸው ታገሰ"
|